የሀምበርቾ 777 ደረጃዎችን ይዘቱንና ታሪካዊ ዳራውን በጠበቀ መልኩ ተጨማሪ ደረጃዎችን ለመስራትና የኢኮ ቱሪዝም ሥራዎችን የበለጠ በማልማት ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የተቋቋመ ኮሚቴ በተዘጋጀው እቅድ ላይ ተወያይቶ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለፀ።

ኮሚቴዎቹ ሀምበርቾን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማልማት እንዲያስችል በተዘጋጀው እቅድ ላይ ተወያይቶ የጋራ አቋም በመያዝ ከሰኔ 2/2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲገቡ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አረጋ እሸቱ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አረጋ እሸቱ በሀምበርቾ ላይ የተሰራውን ዘመን ተሻጋሪ ሥራ የበለጠ በማላቅ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት ይገባል ብለዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀምበርቾን ከጎበኙ ወዲህ የተፈጠረውን ተጨማሪ እድል በመጠቀም በተራራ ላይ የ777 ይዘቱንና ታሪካዊ ዳራውን በጠበቀ መልኩ ደረጃዎችን፣ ማረፊያዎችን፣ መፀዳጃ ቦታዎች፣ መታሰቢያ ቦታዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችና አረንጓዴ መዝናኛ ቦታዎችን ውበት እንዲኖረው ተደርጎ በአጭር ጊዜ ለመሥራት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ነው የገለፁት ክቡር ዋና አስተዳዳሪው።

ሀምበሪቾ የዞኑ ህዝብ ማንነት መገለጫ መሆኑን በመገንዘብ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉ የዞኑ ተወላጆችና የልማት ደጋፊዎች የገንዘብ፣ የጉልበት ፣የዓይነትና የእውቀት ሀብት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ከግለሰብ እስከ ተቋማት ድረስ በማሳተፍ ተራራውን የበለጠ ማልማት ይገባል ያሉት ክቡር አቶ አረጋ እሸቱ በዚህ ታሪካዊና ትውልድ ተሻጋሪ ሥራ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል አሻራውን እንዲያስቀምጥ ጥሪያቸውን ከወዲሁ አቅርበዋል።

የከምባታ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተክሌ ስዩም ሀምበርቾ ተራራን ማልማትና ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ እንዲሆን ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ከሁሉም ማህበራዊ መሠረቶች ለልማቱ የሚሆን ገቢ በመሰብሰብ በአምበርቾ ተራራ ላይ ቀሪ ደረጃዎች ለመገንባትና በሀገር አቀፍ ብሎም ዓለም አቀፍ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን በትኩረት መሠራት አለበትም ብለዋል።

በተራራው ላይ የተለያዩ የቱሪስት መስህብ ሥፍራዎችን በመገንባት ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተክሌ ስዩም ሀምበርቾ ተራራን በሁሉም በኩል ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠርና ጥበቃዎችን ማጠናከር ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ጉዳይ መሆኑንም አክለዋል ገልጸዋል።

በመድረኩ የከምባታ ዞን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ አስካለ ሰሶ፣የከምባታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ሄራሞ፣ የከምባታ ህዝብ ልማት ማህበር የሥራ ኃላፊዎች፣ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ ማስተር አብነት ከበደ፣ በአርክተክት ሙያ የከባተ ልምድ ያላቸው ዲዛይነሮችን ጨምሮ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *