የከምባታ ህዝቦች ልማት ማህበር የሂጋ ሞዴል አዳሪ ትምህርትን በዘላቂነት ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታዎች ዙሪያ ከተማሪ ወላጆች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
ልማት ማህበሩ ትምህርት ቤቱን ለማጠናከር ለተማሪዎች አስፈላጊውን ግብዓት ለማሟላት ከተማሪ ወላጆች ጋር በቅንጅት በተሠራው ሥራ ከ280 ሺህ ብር በላይ በመሰብሰብ ልዩ ልዩ መጠቀሻ መጽሐፍት በልማት ማኀበሩ በኩል ግዥ ተፈጽሞ ለተማሪዎች ንባብ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርጓል።
ልማት ማህበሩ በተላይም በትምህርቱ ዘርፍ የተማረ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ትምህርት ቤቱን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተደረጋ ባለው ርብርብ የተማሪ ወላጆችንና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል።
በመድረኩ የከምባታ ህዝቦች ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ላምቤቦ፣ የልማት ማኅበሩ የትምህርት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አበበ ቦቄ፣ የሂጋ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳ ሶደኖ፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተመስገን ዳንኤልን ጨምሮ የተማሪ ወላጆችና የትምህርት ቤቱ መምህራን ተገኝተዋል





