በሀዋሳ ከተማ እና ዙሪያ አከባቢ ከሚኖሩ የዞኑ ተወላጆች ጋር በዞኑ ልማት ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ ውይይት ተካሄደ
“የከምባታ ህዝብ ልማት ማህበርን በማጠናከር የህዝባችንን ፍላጎትና ጥያቄ ተከትለን በመሥራት ፤ በአንድነት ዘላቂ ልማት በማስመዝገብ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንሸጋገራለን” የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳደሪ
የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ በሀዋሳ ከተማ እና ዙሪያ አከባቢ ከሚኖሩ የዞኑ ተወላጆች ጋር በዞኑ ልማት ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ ውይይት አካሄደዋል።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ እንደተናገሩት የከምባታ ህዝብ ልማት ማህበር የዞኑ ህዝቦች አንድነትና የልማት ተጠቃሚነትን በማጠነከር በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በአዲሱ በጀት ዓመት ለመሳካት መታቀዱን ገልፀዋል።
የሁሉም ወገን አስፈለጊነት በማመን ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ያጣናቸውን ማንኛውንም ነገር የህዝባችንን የልብ አንድነት በማጠናከር ልማቱን መስቀጠል እንችላለን ያሉት የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ ሁሉም የሚያነሰው ሀሳብ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ሰዎች መደመጥ ያለባቸው በያዙት እና በሚያቀርቡት ሀሳብ መሆኑን በመቀበል የጋራ ዞናችንን በተባበረ ልማት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ የዞኑ ማህበረሰብ ከፍተኛ የለውጥ ስሜት በመኖሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰሩ በመሆናቸው የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪው ዞናዊ አንድነትን በማጠናከር የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን ለመመስ በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሆነም ገልፀዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው በበኩላቸው ህዝቡ በልማት ማህበሩ ላይ ያለውን ተሳትፎ ከፍ በማድረግና የህዝባችንን የልማት ጥያቄዎችን በመመለስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መሥራት አለብን ብለዋል።
የሚጠቅመን አንድነትን በማጠቀር በሁሉም አከባቢ ልማት በማምጣት የዞኑን ህዝብ ልማት ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
ሁላችንም በዞኑ በሚሰሩ የልማት ስራዎች አምባሳደር በመሆን እና የተሻለ አንድነት በማምጣት የዞኑን ሁለንተናዊ ልማት ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
የከምባታ ህዝብ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ገ/ክርስቶስ ኑሪዬ በበኩላቸው የህዝባችን ጥያቄዎች መመለስ የሚቻለው የህዝባችንን አንድነትና የልማት ተሳትፎ ማረጋገጥ ስንችል ነው ያሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ህዝባችንን አንድ በማድረግ በማሰባሰብ ወደ ልማት ማስገባት እንዲንችል የከምባታ ህዝብ ልማት ማህበር ተቋሙን ተባብሮ ማጠነከር ያስፈልጋል ብለዋል።
በመድረኩ በዞኑ የተጀመሩ የልማት እንቅስቃሴዎች የተሻሉ እንደሆነ በማንሳት ቀጣይነት እንዲኖራቸው የዞኑ ተወላጆች በቅንጅት መስረት ያስፈልጋል ብለዋል።
በውይይት መድረኩ የከምባታ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ ስዩም ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የክልሉ የስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ ሠርካለም ሳሙኤል የከምባታ ህዝብ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ሎምቤቦ የከምባታ ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ፣ የከምባታ ልማት ማህበር ማኔጅመንት አባላት ፣በሀዋሳ ከተማ እና ዙሪያ አከባቢ የሚኖሩ የዞኑ ተወላጆች በተገኙበት በውይይት መድረኩ ተገኝተዋል።







